የቱርክ ፕሬዚዳንት ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ያሲን አከታይ ጀማል ኻሾግጂ ከተገደለ በኋላ አስክሬኑን በመቆራረጥ በአሲድ አንዲቀልጥ ተደርጓል

Breaking News Politics

የቱርክ ፕሬዚዳንት ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ያሲን አከታይ ጀማል ኻሾግጂ ከተገደለ በኋላ አስክሬኑን በመቆራረጥ በአሲድ አንዲቀልጥ ተደርጓል ብለን እናምናለን አሉ።
የሳዑዲው ጋዜጠኛ ኢስታንቡል ውስጥ ከተገደለ በኋላ የተፈጸመበትን ወንጀል ለመሸሸግ አስክሬኑ እንዳይገኝ ስለመደረጉ ከድምዳሜ ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ከአንድ ወር በፊት የሳዑዲ መሪዎችን በመተቸት የሚታወቀው ኻሾግጂ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ቀንስል ጽ/ቤት ውስጥ መገደሉ ይታወሳል።
• «ኻሾግጂ አደገኛ ሰው ነበር» የሳዑዲው ልዑል
የኻሾግጂ አስክሬን በአሲድ እንዲቀልጥ መደረጉን የሚያሳይ ምንም አይነት የምርመራ ውጤት ግን እስካሁን አልተገኘም።
”የኻሾግጂን አስክሬን የቆራረጡት በአሲድ ለማቅለጥ እንዲመች ነው” ሲሉ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ሁሪያት ለተሰኘ ዕለታዊ ጋዜጣ ተናግረዋል።
”አስክሬኑን መቆራረጥ ብቻ አይደለም፤ እንዲተንም ጭምር አድርገውታል” ሲሉ ያሲን አከታይ ተናግረዋል
ምነጭ፡- ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *