ደቡብ ሱዳን በኩል 502 የድሽቃና የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶች

Uncategorized

22/2011 በደቡብ ሱዳን በኩል 502 የድሽቃና የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይቶች ወደ ሃገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ጋምቤላ ክልል ውስጥ መያዛቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በፌዴራል ፖሊስ የምዕራብ ዲቪዥን ሶስተኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ኢንስፔክተር ተረፈ በለጠ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ጥይቶች የተያዙት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ አማካኝነት ጥቅምት 18 እና 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው።

ከተያዙት ጥይቶች መካከልም 79ኙ የዲሽቃ ሲሆኑ ቀሪዎቹ የክላሽንኮቭ መሆናቸውን የገለጹት ኢንስፔክተሩ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችም ተይዘው በምርመራ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *